5ተኛ ዙር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የወጣቶች ኮንፈረንስ በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) 5ተኛ ዙር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የወጣቶች ኮንፈረንስ በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ነው።
በአዲስ መልክ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ባለው ክልል አቀፍ የወጣቶች ኮንግረስ ከክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቴ ገለፃ ወጣቱ በሀገር የነገ ተግባር ላይ አበርክቶው የጎላ መሆኑን አንስተው በተለይ ሰላምን በማስፈን ላይ ጉልህ ሚናው መሆኑን ተናግረዋል።
ለአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላምና ብልፅግና የወጣቱ ሚና የጎላ ነው ያሉት ኃላፊው ይህ መድረክም የወጣቱን ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆን እንደሚያስችልም ተናግረዋል።
በመድረኩ በመገኘት የወጣቶቹ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገለፃ ክልሉ በርካታ ሀብት ያለውና ለሀገርም የሚኖረው ሚና ትልቅ መሆኑን አንስተው ለዚህ ተግባር መሳካትም የወጣቱ ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
በሀገረ መንግስት ግንባታ ወጣቱ የሚጫወተው ሚና ሊጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አንተነህ በተለይ ወጣቶች ያሏቸውን በርካታ ጥያቄዎች በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባቸው ገልፀው ክልሉም የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩም ወጣቱ በሀገረ መንግስት ግንባታ ስላለው ሚና የሚዳስስ ፁሁፍ ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ቃለአብ ፀጋዬ
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከ136 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ እንዲሻሻል ማስቻሉን አስታወቀ
በበዓላት ወቅት በሚፈጸሙ የእርድ ስነ-ስርዓት ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ