የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ዲላ ከተማ ገቡ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ዲላ ከተማ ገቡ

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልዑክ ወደ ከተማዋ ሲደርሱ በጌዴኦ ዞን እና የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የግብርና እና ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የክልል ቢሮዎች መቀመጫ የሆነችው የዲላ ከተማ ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ወደ ከተማዋ ሲደርሱ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ፣ የቀድሞ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዮት ደምሴ እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዘጋቢ፡ አብደላ በድሩ