መገናኛ ብዙሐን ለብሔራዊ ምክክር መሣካት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) መገናኛ ብዙሐን ለብሔራዊ ምክክር መሣካት የበኩላቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት አሳሰበ።
ተቋሙ በብሔራዊ ምክክር እና በጋዜጠኝነት ስነ ምግባር መርሆዎች ዙሪያ ለጋዜጠኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች በሚሠሯቸው ዘገባዎች ለአገራዊ አንድነት ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ተብሏል።
ጋዜጠኞች ከየትኛውም ተጽዕኖ ነጻ ሆነው በሚዛናዊነትንና ገለልተኛነት መርህ ተከትለው መሥራት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት አታላይ አሳስበዋል።
የመገናኛ ብዙሐን የሚያሰራጯቸው መረጃዎች ሚዛናዊ እና ገለልተኛ ሆነው ለአገራዊ አንድነት እና ሠላም መጠበቅ ፋይዳ ያላቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ስልጠና የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህር ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ ናቸው።
በስልጠና መድረኩ ላይ ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪን ድርጅት አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ፣ ከወላይታ ቴሌቪዥን እና ከኢዜአ የተጋበዙ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሣታፊ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከ136 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ እንዲሻሻል ማስቻሉን አስታወቀ
በበዓላት ወቅት በሚፈጸሙ የእርድ ስነ-ስርዓት ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ