የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጎፋ ዞን ገቡ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጎፋ ዞን ገቡ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የደቡብ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጎፋ ዞን ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ዛላ ወረዳ ሲደርሱ የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዘጋቢ፡ አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን