ውጤታማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ለማከናወን ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል- የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር

ውጤታማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ለማከናወን ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል- የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ውጤታማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ለማከናወን ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ እንደሚገባ የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር አሳሰበ፡፡

የዘንድሮውን የወጣቶች የክረም ወራት በጎ ፈቃድ አገለግሎት አስመልክተው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዞኑ 2015 በጀት ዓመት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገለግሎት ለማከናወን የ2014 አፈፃፀም በመገመገም ወደ ተግባር መገባቱን የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ቀበሌ መንገሻ አስታውቀዋል፡፡

በመርሀግብሩ ከ10 በላይ የሆኑ የተለያዩ ተግባራቶች ይከወናሉ ያሉት ኃላፊው የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ በትኩረት የሚሠራበት መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

አመራሩ ለተግባሩ ዕገዛ በማድረግ በኩል ከዞን ጀምሮ ከተሠራ በየዘርፉ እምርታዊ ለውጥን ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ- ከሚዛን ጣቢያችን