በኬሚካል ኢንዱስትሪ የጎማ ዛፍ ልማትና ፕሮጀክት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ የጎማ ዛፍ ልማትና ፕሮጀክት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ የጎማ ዛፍ ልማትና ፕሮጀክት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተወካይ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ÷ ሃገር በቀልና የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸዉ ችግኞች መተከላቸዉን ገልፀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፕሮጀክቱ አመራሮችና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱም 2 ሺህ ችግኞችን መትከል መቻሉን አስረድተዋል።

ችግኞችን መትከል ለትዉልድ ቅርስን የማኖር ተግባር መሆኑን የገለፁት ኃላፊዉ የተተከሉትን ችግኞች የፅድቀት ደረጃን መከታተልና የመንከባከብ ተግባርም በትኩረት ይከናወናል ብለዋል።

በዕለቱ ካነጋገርናቸዉ የፕሮጀክቱ ሰራተኞች መካከል አቶ ታደሰ አባይነህ እና ወይዘሮ መረሃዊ ሀዱሽ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸዉ መደሰታቸዉን ገልፀዉ ቀጣይ ችግኞቹን በመንከባከብ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ዘጋቢ፡ ዮሐንስ አሰፋ – ከሚዛን ጣቢያችን