ዳይመንድ ሊግ ዛሬ ምሽት በሞናኮ ከተማ ይካሄዳል

ዳይመንድ ሊግ ዛሬ ምሽት በሞናኮ ከተማ ይካሄዳል

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ጨምሮ የበርካታ ሃገራት አትሌቶች በ14 የተለያዩ የሜዳላይ ተግባራት እና ርቀቶች ይሳተፋሉ።

በ5000 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል በሪሁ አረጋዊ፣ ሃጎስ ገብረህይወት፣ ሳሙኤል ተፈራ፣ ኩማ ግርማ እና ጥላሁን በቀለ ይወዳደራሉ።

በተጨማሪ ዩጋንዳዊዉ አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ፣ ኬኒያዊዉ ኒኮላስ ኪፕኮሪር፣ ስፔናዊዉ ሞሃመድ ካቲር እና ለጣሊያን የሚሮጠዉ የማነ ብርሃን ክሪፓ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ።

በሴቶች ማይል እርቀት ከኢትዮጵያውያን አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ በብቸኝነት ትሳተፋለች።

በቅርቡ የ1500 ሜትር እና 5000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በእጇ ያስገባችው ኬኒያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕየጎን በአንድ ዓመት ዉስጥ ሶስት የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር እያለመች በርቀቱ ትሳተፋለች።

አትሌቷ በርቀቱ 4:16.71 የግሏ ምርጥ ሰዓት ሲሆን ክብረ ወሰኑን ሲፋን ሃሰን በ2019 ሄርኩሊስ ላይ በተደረገ ዉድድር 4:12.33 በመግባት እስካሁን ተቆጣጥራለች። የኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊዋ ላዉራ ሙኢር፣ አዉስትራሊያዊቷ አትሌት ጄሲካ ሃል እና አሜሪካዊቷ ኒኪ ሂልትዝ ሌሎች ጠንካራ ተወዳዳሪዎች ናቸው።

በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል አብርሃም ስሜ እና ሳሙኤል ተፈራ ከኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ናቸዉ።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ