ነገ የቻልኩትን ያህል ችግኝ እተክላለሁ – ህፃን እሱባለው

ነገ የቻልኩትን ያህል ችግኝ እተክላለሁ – ህፃን እሱባለው

ነገ በሚተከለው የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተሳታፊ ለመሆን መዘጋጀቱን በወላይታ ሶዶ ከተማ ያገኘነው ህፃን እሱባለው ደጉ ነግሮናል::

ህፃን እሱባለው 12 ዓመቱ ሲሆን የ5ኛ ክፍል ተማሪ ነው::

ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ አርንጓዴ ሆና ማየት እፈልጋለሁ የሚለው ታዳጊው፥ በእሱ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ህፃናት ነገ በችግኝ ተከላው ላይ በመሳተፍ ለሀገራቸው መልካም ነገር ቢሰሩ ጥሩ ይሆናል ሲል አስተያየቱን ሰጥቶናል::

ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ