የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆን በመጀመራቸው ተደስተዋል – በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ነዋሪዎች
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆን በመጀመራቸው መደሰታቸውን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን የአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ከረጂ ድርጅት ባገኘው 90 ሚሊየን ብር ያሰገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስመርቆ አገልግሎት ጀምሯል፡፡
አቶ አየለ አገሎና አቶ ተክሌ ኃይሌ ሚካኤል በዞኑ የአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆን በመጀመራቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
የውሃው መገንባት ትናንት ይደርሰባቸው የነበረውን ዕንግልትና አላሰፈላጊ ወጪ ከመቀነስ ባለፈ በአግባቡ የእለት ተግባራቸውን በመከወን ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡
በምረቃ-ሰነ ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕስ መሰተዳደር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሸ ዋጌሾ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ህዝቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡
የውሃ ግንባታው 90 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ የተገነባ ሲሆን በተደረገው ርብርብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር በየነ በላቸው ናቸው፡፡
ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ሃላፊው ህብረተሰቡ ግንባታውን በአግባቡ በመያዝና በመንከባከብ መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ቀሪ የውሃ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ የክልሉን ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ኢንጂነር በየነ አክለዋል፡፡
የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ እውን በመሆኑ ፋይዳው ላቅ ነው ያሉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞና የአንድራቻ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ሸሎ አደሎ ከ11 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የነጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡
በምረቃው ስነስርዓት ላይ የፌዴራል ውሃ ልማት ፈንድ ዋና ሰራ አሰፈጻሚ አሰፈጻሚው አቶ ዶጊሶ ጎና እና የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሸማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ በክልሉ የሚገኙ የየተለያዩ ብሔሮች ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አት ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አደረጉ
300 ለሚሆኑ ወላጅ አጥ ተማሪዎች ኢትዮ- ቴሌኮም ሳውላ ድስትሪክት ከ270 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ