በወጪና ገቢ ንግድ ረገድ የነበረው የሚዛን መዛባት መሻሻል አሳይቷል – ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

በወጪና ገቢ ንግድ ረገድ የነበረው የሚዛን መዛባት መሻሻል አሳይቷል – ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መዛባት አምና ከነበረበት 13 በመቶ ወደ 9 ነጥብ 8 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በ28ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እደገለጹት በወጪና ገቢ ንግድ በኩል ይስተዋል የነበረው የሚዛን መዛባት መሻሻል አሳይቷል፡፡

የወጪ ንግድ በሸቀጦች 11 በመቶ ከአምናው አንጻር ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

በአገልግሎት በ10 ወራት ውስጥ 14 በመቶ እድገት መታየቱንም አስታውቀዋል፡፡

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ደግሞ 10 ነጥብ 4 በመቶ አድጓል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ በማብራሪያቸው፡፡

የገቢ ንግድን በተመለከተ ከ15 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ይህም ከአምናው አንጻር 3 በመቶ ቀንሷል ብለዋል፡፡

በገቢ ንግድ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ስንዴ፣ ሩዝና የድንጋይ ከሰል መቀነስ በመቻላቸው የተመዘገበ ለውጥ ነው ብለዋል፡፡