“ልማትን ነገ አለማለሁ ማለት አያስፈልግም” – አቶ ተስፋዬ ታከለ

በማቱሳላ ኃይሉ

የዛሬው ባለታሪካችን አቶ ተስፋዬ ታከለ ይባላሉ፡፡ የተወለዱት በ1961 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሽሮ ሜዳ በሚባል አካባቢ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተማሩት በድሮ ስሙ “ማርስታ” በአሁን ደግሞ እንጦጦ አምባ በሚባል ትምህርት ቤት ነው። ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል አዲስ አበባ በሚገኘው የካቲት 12 ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡

በወቅቱ በነበረው የደርግ ስርዓት ወጣቶች ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄዱ የሚገደዱበት ስለነበር በሽሽት ምክንያት ወደ ወላጆቻቸው የትውልድ አካባቢ ደቡብ ክልል በመምጣት ሥራ ለማፈላለግ ተገደዱ።

በመቀጠልም አርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅን በመቀላቀል በመምህርነት ሙያ ተመርቀው ሥራ ጀመሩ፡፡ በሙያውም ከ1981 እስከ 2003 ዓ.ም አገልግለዋል። በአሁኑ ሰዓት ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት መሆናቸውን በነበረን ቆይታ አጫውተውናል፡፡

በ1979 ዓ.ም ወደ ጋሞ ዞን በማቅናት መኖር የጀመሩት ባለታሪካችን በ1981 ዓ.ም በመምህርነት ከጀመሩት ሥራ ጎን ለጎን በጽሕፈት መሳሪያ፣ በእንጨት ሥራና በሌሎችም ንግዶች ሲተዳደሩ መቆየታቸውን ይገልጻሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ገቢያቸውን በማሳደግ አንቱታን ካተረፉ ባለሃብቶች ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው በሰላም በር ከተማው በ17 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ካፒታል የእንግዳ ማረፊያ ህንፃ ግንባታ ላይ መሆናቸው ነው፡፡ በእስካሁኑ ሂደት 10 ሚሊዮን ብር የፈጀውን የግንባታ ስራ ማጠናቀቃቸውንና ግንባታውን በቅርብ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተጉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከዚህ ጐን ለጐን በትርፍ ሰዓታቸው ከባለቤታቸው ጋር በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው ለውጤታማነት እየሰሩ ነው፡፡

ከ2003 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የመንግሥትን ሥራ አቁመው ወደ ንግድ መግባታቸውን የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ የሰው ልጅ ጠንክሮ ከሠራ ወዳለመው የስኬት ከፍታ ከመውጣት የሚከለክለው ነገር እንደሌለ እኔ ማሳያ ነኝ ሲሉ ይመሰክራሉ፡፡

ይሁን እንጂ ሁሉም ሥራ ሲጀመር መንገድ ሁሉ አልጋ በአልጋ እንደማይሆን የሚናገሩት ባለታሪካችን የግል ሥራ ጅማሪያቸው ተግዳሮት በገጠመው ሰዓት ከቤተሰብ ያገኙት የገንዘብ እገዛ መንገዱን እንዳቀናላቸው አልሸሸጉም፡፡

በዚህም “ለረጅም ዓመታት ስመኘው የነበረውን አካባቢውን የማልማት ምኞቴ በማሳካት ወደቀጣይ የሥራ ዕቅዴ በሙሉ ልብ ለማምራት ነው” ሲሉም ቀጣይ ከዚህ የበለጠ ህልም እንዳላቸው የዕቅዳቸውን ሰበዝ በጨረፍታ ስበው አመላክተዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ ለህንፃ ግንባታው የሠላም በር ከተማ ማዘጋጃን መሬት በሚጠይቁበት ወቅት ያቀረቡት ፕሮጀክትና ያስገቡት ካፒታል ያልተመጣጠነ ነው በሚል “ይህ ሰው እውነት ቦታ ቢያገኝ እውነት ፕሮጀክቱን ያሳካል?” የሚል ጥርጣሬ አዘል ጥያቄ ተነስቶባቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። በዚህም ቦታ ሳያገኙ የቆዩባቸው ጊዜያት መኖራቸውን በማስታወስ ፈገግ ብለው በቁጭት ይናገራሉ፡፡

አሁን ግንባታ የመጀመሩበት ቦታን ከማግኘታቸው በፊት 4 እና 5 ጊዜ ያህል የከተማውን ማዘጋጃና የሚመለከታቸውን የሥራ ኃላፊዎች ለማግኘት ደጅ መጥናታቸውን ጠቁመው የሰው ልጅ ያሰበውን ከማድረግ ወደኋላ አይልምና ዛሬ እዚህ ደረጃ በመድረሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ያወሳሉ፡፡

በኋላ ላይ ግን ይላሉ ባለታሪካችን ካስመዘገቡት ካፒታል ባለፈ፤ ጥረት እና ትጋታቸውን የተመለከተው የከተማ ማዘጋጃ ቤት ከገዙት ቦታ በተጨማሪ ኩታ ገጠም ላይ የነበረውን መሬት እንዲሰሩበት በመሥጠት ለኢንቨስትመንታቸው ተጨማሪ አቅም እንደሆናቸው አልሸሸጉም፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሠላም በር ከተማን ከወላይታ እና ጎፋ ጋር የሚያገናኘው የአስፋልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎችም ወደዚህ ከተማ በመምጣት ቢሰሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ ተናግረዋል። የመንገዱ መገንባት ደግሞ የሠላም በር ከተማን ልዩ ውበት እንደሚያጎናፅፋት ያላቸውን እምነት ጭምር ገልፀዋል። ስለዚህ ገንዘብ ያላቸው ባለሀብቶች ገንዘባቸውን አውጥተው ለበርካቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር እራሳቸውንም ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ በመረዳት በከተማው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት አቶ ተስፋዬ እያስገነቡ ያሉት የእንግዳ ማረፊያ ለ12 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መሥጠት ሲጀምር ደግሞ ለበርካቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ አማራጭ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡

ባለታሪካችን አቶ ተስፋዬ ምንም እንኳን ውልደታቸው አዲስ አበባ ቢሆንም መኖሪያ ያደረጉበት የሠላም በር ከተማን ሙቀትና ሌሎች ተግዳሮቶችን ተቋቁመው መሥራታቸው ለሌሎች በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ከተማው ከአዲሰአበባ አንፃር በብዙ እጥፍ ማደግ የሚቀረው ቢሆንም በማይመች ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል አብነት ተደርገው እንዲጠቀሱ የሚያደርግ ነው፡፡

ለዚህ ምክንያቱ ምን ይሆን ስንል መጠየቃችን አልቀረምና ባለታሪካችን ሲመልሱ፡- “ያደኩት በድህነት ውስጥ ነው። ከልጅነቴ ጀምሮ ግን ሃብታም የመሆን ምኞት ስለነበረኝ፤ ዶሮ በማርባት እና መሰል ሥራዎች ተሰማርቼ ገንዘብ ለማግኘት እሞክር ነበር፡፡ የልብን አይቶ የማይነሳው ፈጣሪ ደግሞ ወደዚህ አካባቢ እንድመጣ ወቅቱን ምክንያት አድርጎ ልኮ ይኸው ለዛሬ ክብር እንድበቃ አድርጎኛል።

“ህልሜ የሠላም በር ከተማን እንደ አርባ ምንጭና ሌሎች ያደጉ ከተሞች የማሳደግና የማሳመር ዕቅድ አለኝ፡፡ በዚህም ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ወጣት በአቅራቢያ ያሉ አማራጮችን በመጠቀም ለለውጥ እንዲነሳሳ ለማድረግ ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም መሥራት የሚችሉ ወጣቶች አካባቢው ነገ ሲያድግ እሠራለሁ ብለው መቀመጥ የለባቸውም የሚሉት ባለታሪካችን እነሱ ቀድመው በመሥራት ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ጠቃሚ ዜጎች ሊሆኑ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡