በክልሉ ከ2 መቶ 32 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆናቸዉ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 16/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ከ2 መቶ 32 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆናቸዉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያህዝቦች ክልል የህብረት ስራ ኤጀንስ ገለፀ።
ኤጀንስዉ “ጠንካራ የህብረት ሰራ ማህበራት ለሀገራዊ ልማት” በሚል መሪ ቃል የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ የ2015 አፈፃፀም ግምገማና የህብረት ስራ ማህበራት ቤተሰብ ጋር የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂደዋል።
የክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ተገኝ በምክክር በመድረኩ ላይ እንደገለፁት በክልሉ በምርትና አገልግሎት ዘርፎች የተደራጁ ከ2 ሺህ በላይ መሠረታዊ የህብረተሰብ ማህበራትና ከ20 በላይ ዩኒየን መቋቋማቸውን ገልፀዋል።
በዚህም ከ2 መቶ 32 ሺህ በላይ የክልሉ ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ በበኩላቸው የህብረት ስራ ማህበራት ለሀገራችን የኢኮኖሚ ልማትና ዕድገት ሚናቸዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ በተለይም በማዕድንና በግብርናው ዘርፍ የተደራጁ የህብረት ስራና ማህበራትን አቅም በማጎልበት በኩልም የክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፍዎች የህብረት ስራ ማህበራት የሚጠበቅባቸዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚናን በተገቢዉ መንገድ እንዲወጡ ከኤጄንሲዉ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን በአስተያየታቸዉ አረጋግጠዋል።
በዕለቱ የህብረት ስራ ማህበራት ቤተሰብ ፎረም ምስረታ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ አሰፋ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ በክልሉ የሚገኙ የየተለያዩ ብሔሮች ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አት ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አደረጉ
300 ለሚሆኑ ወላጅ አጥ ተማሪዎች ኢትዮ- ቴሌኮም ሳውላ ድስትሪክት ከ270 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ