ለሀገረ-መንግስት ግንባታ በሚጠቅሙና በጋራ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገራዊ ምክክር

ለሀገረ-መንግስት ግንባታ በሚጠቅሙና በጋራ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሂደት የተሳካ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን – በካፋ ዞን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች

ሀዋሳ፡ ሰኔ 16/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለሀገረ-መንግስት ግንባታ የሚጠቅሙና በጋራ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሂደት የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ በካፋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንቅስቃሴ የሕዝቡ ተሳትፎ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎና ኮሚሽነር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የነበሩ የሀገሪቱ መንግስታት አጀንዳቸውን ከላይ ወደታች ከማፍሰስ ውጭ ከሕዝቡ ጋር ምክክር ባለማድረጋቸው አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሷን የሚገልጹት የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ምክክሩ ደግሞ ለልማትና ለሰላም ግንባታ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ለሀገረ-መንግስት ግንባታ የሚጠቅሙና በጋራ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሂደት የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ  ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር ለተባባሪ አካላት ስልጠና መሰጠቱን የገለጹት ኮሚሽነር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ አሁን ደግሞ የተወካዮች ምልመላ በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸው ሂደቱ በመልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በነበረው ሂደት ተስፋ ሰጪ ነገሮችን መመልከታቸውን የገለጹት የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ አጀንዳዎች የሚቀረጹት ደግሞ የውክልና ሥርዓትን ተከትሎ ሕዝቡን በማሳተፍ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሌሎች ሀገሮች የሚለይበትን ሂደት አጀንዳው የሚቀረጸው ከሕዝቡ ሲሆን የአሰያየም ሂደቱ ደግሞ ገለልተኛ ነው ብለዋል፡፡

ከማንም ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ ሁኔታ የሚደረገው ሂደት ቅቡልነት ያለውን መንግስት ለመመስረትና ለሀገር ግንባታ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል ኮሚሽነር ሙሉጌታ፡፡

የምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን ሕዝቡ እያደረገ ያለው ተነሳሽነት አበረታች መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር ሙሉጌታ በሂደቱ የሚታዩ ክፍቶች ሲኖሩ ደግሞ እርማት የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ የአወያዮች ምልመላ የሚደረግ ሲሆን ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን ሕዝቡን ማዳመጥ የሚችሉ፣ በስነ-ምግባራቸውና በስብዕናቸው በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሊመለመሉ እንደሚገባም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡ መለሰ ገብሬ – ከቦንጋ ጣቢያችን