ምክር ቤቱ 25ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል

ምክር ቤቱ 25ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል

ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው 25ኛ መደበኛ ጉባዔው የ24ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

የምክር ቤቱ ቀጣይ አጀንዳ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት