በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ በተደጋጋሚ በአርብቶና አርሶ አደር መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ መጨረስ የሚያስችል ባህላዊ ዕርቀ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ: ሰኔ 13/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ በተደጋጋሚ በአርብቶና አርሶ አደር መሐል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ መጨረስ የሚያስችል ባህላዊ ዕርቀ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
በሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በሳላማጎ ወረዳ ሙርሲ፣ ቦዲ፣ ዲሜና ባጫ ብሔረሰቦች በጋራ ተቻችለውና ተፈቃቅረው የሚኖሩ ሲሆን አልፎ አልፎ በጥቂት ምክንያቶች አለመግባባት ተፈጥሮ የንብረት ውድመትና ለሰው ልጅ ሞት መንስኤ ሲሆን ይስተዋላል።
ይህ ደግሞ በተደጋጋሚ የሚከሰት መሆኑ በአካባቢው ዘላቂ ዕርቀ ሠላም በማስፈለጉ ሁሉ አቀፍ ባህላዊ ዕርቀ ሠላም ሥነ ሥርዓት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከ136 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ እንዲሻሻል ማስቻሉን አስታወቀ
በበዓላት ወቅት በሚፈጸሙ የእርድ ስነ-ስርዓት ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ