በወላይታ ዞን ድጋሚ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሠላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል – አቶ ተስፋዬ ጎአ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን ድጋሚ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሠላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን የወላይታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎአ ገለፁ::
አቶ ተስፋዬ በተለይም ለደሬቴድ እንደተናገሩት በወላይታ ዞን ዳግም በሚካሄደው የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ የመምረጥ መብቱን ተጠቅሞ በነቂስ መሳተፍ እንዲችል የፀጥታው መዋቅር የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቋል ነው ያሉት::
በዕለቱ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዳይጠቀም በተለያየ መንገድ የማደናቀፍ ሥራ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ካሉ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ሠላማዊነት፣ ፍትሀዊነት እና ዴሞክራሲያዊነት የድርሻውን እንዲያበረክት ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል::
ዘጋቢ: ማሬ ቃጦ
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ በክልሉ የሚገኙ የየተለያዩ ብሔሮች ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አት ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አደረጉ
300 ለሚሆኑ ወላጅ አጥ ተማሪዎች ኢትዮ- ቴሌኮም ሳውላ ድስትሪክት ከ270 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ