ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች ገለጻ አድርገዋል።

በመድረኩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መገኘታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የውይይ መድረኩ የበለፀጉ ከተሞችን ለመፍጠር ከንቲባዎች በሚጫወቱት ሚና ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡