የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በወዳጅነት አደባባይ ሽኝት ተደረገለት

 የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ ተከናወነ።

የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን  በማርሽ ቡድን፣ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እና በስራ ባልደረቦቻቸው ታጅቦ ወዳጅነት አደባባይ ደርሷል።

በወዳጅነት አደባባይም÷ የአቶ ግርማ የሺጥላ ባልደረቦች ፣ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች አሸኛኘት አድርገዋል።

በመቀጠልም የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በወላጆቻቸው ፍላጎት እና ጥያቄ መሰረት በተወለዱበት ሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ እንደሚፈጸም ተገልጿል።