ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ በቱሪዝሙ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ሥምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው በትብብር የሚሠሩት፡፡

በጉዳዩ ላይ በቱሪዝም ሚኒስቴር የፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ዳዊት ከኮሎምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽሕት ቤት ኃላፊ አንጀሊካ ጉቴሬዝ ጋር መምከራቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡