በዛምቢያ ንዶላ እየተካሄደ ባለው ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውድድር ዛሬ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
በዚህም አትሌት ውብርስት አስቻለ በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ፣ አትሌት ሳምራዊት ሙሉጌታ 2ኛ በመሆን የብር እንዲሁም አትሌት ምጥን እውነቴ በሦስተኝነት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
በወንዶች ደግሞ ማሞ ኢማና 2ተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ ሳሙኤል ቡቼ 4ኛ ገመቹ ቶሎሳ ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያ 2 ወርቅ ፣3 ብር እና 3 ነሃስ በድምሩ 8 ሜዳሊያ ማስመዝገቧን ከኢትጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
More Stories
ዛሬ ምሽት በአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
የ 2023/24 ዉድድር ዓመት የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት መካሄድ ይጀምራል
ነይማር ጁኒዬር የብራዚል ወንዶች ብሄራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኗል