
ኢትዮጵያና ሩሲያ በመረጃና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በሌሎች መስኮች የሚያደርጉትን ሁሉን አቀፍ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህ ወቅት ዳይሬክተር ጄኔራሉ ሁለቱ ሀገራት የረጅም አመት የታሪክና የባህል ትስስር ያላቸው መሆኑን አስታውሰው፤ ወቅታዊ የኢትዮጵያን ፈተና ለማሻገር እገዛ በሚያደርጉ መስኮች ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ፕሮፌሽናል ተቋም ለመገንባት እያከናወናቸው ላሉ ተግባራት ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር አቅም እንደሚፈጥርለት የጠቆሙት አቶ ተመስገን፤ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት በችግር ወቅትም ተፈትኖ ፍሬያማ ስኬት የታየበት በመሆኑ በቀጣይም በመረጃና ደህንነት ዘርፍ ትብብሩ ተጠናክሮ ስለሚቀጥልበት ጉዳይ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ በክልሉ የሚገኙ የየተለያዩ ብሔሮች ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አት ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አደረጉ
300 ለሚሆኑ ወላጅ አጥ ተማሪዎች ኢትዮ- ቴሌኮም ሳውላ ድስትሪክት ከ270 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ