ከጎጀብ ማዶ….
የኦሮሚያና ደቡብ ክልል መክፈያ የሆነው የጎጀብ ወንዝ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ይፈሳል ማረፊያውም የኦሞ ወንዝ ነው፡፡ ጉማ ከሚባሉት ተራሮች ተነስቶ ወደ ምስራቅ የሚፈሰው ይህ ወንዝ በጥንት ዘመን ካፋዎች ጋሻ ጭምር እንደነበር ፀሐፍት ያትታሉ፡፡ በዚያ ዘመን የወንዙ ዳርቻ እጅግ ግዙፍና አስፈሪ በሆኑ የዱር እንሰሳት የተሞላ እንደነበር ይነገራል፡፡ ካፋዎችን ወንዝ ለማጥቃት የመጣን ሀይል ወንዙ ብቻ ሳይሆን የማያሻግሩት አስፈሪዎቹ የዱር አራዊቶችም እንደ ነብር፣ አንበሳ፣ ዝሆን፣ ጉማሬ እና ሌሎችም እንሰሳቶች እንደነበሩና እንደቀደመው ዘመን አይሁን እንጂ አሁንም አሻራዎቹን እንዳለቀቀ አይተናል፡፡ ያሁኑን የጎጀብን ዙሪያ መለስ ወደ ቀደመ ማንነቱ ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅ ይሆን?