Read more: የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በደቡብ ምእራብ አካባቢ ያሉትን የቅመማ ቅመም ምርቶችን ወደዘመናዊ የግብይት ስርአት ማስገባቱን አስታወቀ
ተዓምረኛው ቅርጫት
ከዕለታት በአንድ ቀን በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አርሶ አደር ነበር። እርሱም በአካባቢው እንዳሉት አርሶ አደሮች ሁሉ ታታሪ ገበሬ ነበረ። ስራውን ሁሌም በአግባቡ ነው የሚያከናውነው። ከዕለታት በአንዱ ቀን እንደተለመደው ጓሮውን ሲቆፍር የተለየ ነገር ያጋጥመዋል። ያንን ያየውን ነገር ችላ ብሎ አላለፈውም። በደንብ ለማየት ያስችለው ዘንድ ዙሪያውን በጥንቃቄ መቆፈር ቀጠለ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ በሚገባ እየታየው መጣ። ታታሪው ገበሬም ጉጉቱ ይበልጥ እየጨመረ መጣ። ቁፋሮውን አጠናክሮ ቀጠለ። አስቀድሞ ጫፉን ያየው ነገር ግልፅ ብሎ መታየት ጀመረ።
የላስካ ጉዞዬ
ሀገራችን በርካታ ተፈጥሯዊ ቦታዎች አሏት፡፡ ሁሉንም የተፈጥሮ ቦታዎች ማዳረስ ባይቻልም በተገኘው አጋጣሚ ያዩትን ለሌላው በምናብ ማሳየት ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በስራ አጋጣሚ ከባልደረቦቼ ጋር መነሻችን ከሆነችው ሃዋሳ ከተማ ጉዞ ጀምረናል፡፡ አስቀድመን ግን እህል በአፋችን ጣል አድርገን፣ ቡናችንን ተጎንጭተን ነበር ጉዞ የጀመርነው፡፡ እኔ በበኩሌ ጉዞዬን ያጣፍጥልኛል ብዬ አማራጭ የወሰድኩት መጽሃፍ ማንበብ ነበር። አንድም ድካም እንዳይሰማኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለአእምሮዬ እውቀት ለመመገብ፡፡ ማልደን የተነሳንበት ይኸው ጉዞ አየሩ ቀዝቀዝ ስለሚል ድካም እንዳይሰማን አድርጎናል፡፡ ለሐዋሳ ቀረብ የምትለውን ለኩን አልፈን፣ ሞሮቾን ተሻግረን ለጥ ባለው አስፓልት መንገድ ተጉዘን ሶዶ ከተማ ደርሰናል፡፡ ሶዶ ከተማ ስትነሳ አብሯት የሚነሳ አንድ ነገር አለ፡፡ ጥሬ ስጋ፡፡
ከፈራረሱ አገራት በስተጀርባ!
ትክክለኛ ትርጉሙና ያለው ፋይዳ በቅጡ ባልተለየበት ግሎባላይዜሽን ወይንም ሉላዊነት አገራት ሉአላዊነታቸውን እያጡ ለመሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ላለፉት ሁለት አስርተ-ዓመታት በአሜሪካና አውሮፓውያን ዘንድ ብዙ የተባለለት አይዲዮሎጂያዊ አመክንዮ እየተባነነበት ይመስላል፡፡ የጉዳዩን ቅቡልነት ለማጽናት የተካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮችና ጥናቶች ክሹፍ መሆናቸው አስረጅ አያሻውም፡፡ በግሎባላይዜሽን ሰበብ የአገራት ሉአላዊነትን ለመናድ የተሞከሩ ድርጊቶች ብዙዎችን አገር አልባ አድርጓቸዋል፡፡ ዓለምን አንድ የማድረግ ዓላማ የነበረው ግሎባላይዜሽን፥ በአሜሪካና በአውሮፓ እየተከሰቱ ባሉ አዳዲስ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ሳቢያ ጫና ውስጥ ወድቋል፡፡