በይበልጣል ጫኔ
«ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት …» ይላሉ÷ አበው። እንደ አዳም ረታ ሃሳብ ደግሞ÷ «ቡሄ የቂጣ ድልድይ ነው»÷ ሰዎችን ከዘመን ወደ ዘመን የሚያሸጋግር። በቡሄ የሆያሆዬ ዜማ ታጅበን ሙልሙላችንን እየገመጥን አለፍ ስንል÷ በእርግጥም ሰዉ አዲሱን ዓመት ለመቀበል ደፋ ቀና ሲል ማየታችን የተለመደ ነው።
“እንቁ ለጣትሽ”
በመሐሪ አድነው
በየዓመቱ በታላቅ ድምቀትና ስሜት ከምናከብራቸውና ከምንዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጁ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በአዲስ ዓመት መባቻ በወርሃ መስከረም ጋራ ሸንተረሩ በአደይ አበባ ያሸበርቃል፡፡ በአዲስ ዓመት ደግሞ ሠው ሁሉ በአዲስ ተስፋ ይሞላል፡፡ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር መልካም ምኞቱንም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይለዋወጣል፡፡

የኮንታ ዞን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰንጋዎችንና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
ሀዋሳ፡ መስከረም 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የኮንታ ዞን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰንጋዎችንና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
Read more: የኮንታ ዞን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰንጋዎችንና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
እንቁ ዘመን
በአለምሸት ግርማ
“ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን እማማ አሉ ብለን… አባባ አሉ ብለን… አበባ አየሽ ወይ ለምለም...” ስለ አዲስ ዓመት በዓል ሲታሰብ ዘር ኃይማኖት ሳይለይ ከሰው ልብ ውስጥ ዘልቆ የሚገባ ዜማ ነው። አዲስ ዓመት መሆኑን ማልደው የሚያበስሩን ታዳጊ ሴት ልጆች የሚያዜሙት ኢትዮጵያዊ ዜማ “አበባ አየሽ ወይ”። የአዲስ ዓመት በዓል ሲታሰብ ልምላሜ፣ አደይ አበባ፣ የባህል ልብስ፣ የባህል ምግብና መጠጥ ትዝታው ብዙ ብዙ ነው።