የሰው ልጅ ፍላጎቶች እያደጉ ባሉበት በአሁኑ ዓለም እራስን መቻል እንደ ማንነት መገለጫ ሊታይ ይችላል፤ ምክንቱም እርዳታ ጠባቂነት በተቀባዮች ላይ የጥገኝነት ስሜትን ስለሚፈጥር፡፡ ድርቅ፣ ረሀብና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮች በአፍሪካ አህጉር በብዛት ይከሰታሉ። የችግሩ መንስኤና መፍትሄ በባለሙያዎች ከሚገለጸው በላይ ህብረተሰቡንም ሊያነሳ እንደሚገባ ይታመናል፡፡ አፍሪካ እንደ ማንኛውም አህጉር የራሷ መገለጫና ከሌሎች ጋር ያገናኟት መልካም መስተጋብሮች አሏት፡፡