የስደት ሌላ መልኮች
ዓለምን ወደ አንድ መንደርነት ከለወጡ የቴክኖሎጂ እድገትና ፈጠራዎች ባሻገር ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚደረግ ዝውውርና እንቅስቃሴ ይገኝበታል፡፡ ይህ አይነቱ እንቀስቃሴ ስደትና ፍልሰት በሚሉት አተያይ ውስጥ የተለያየ ብያኔ ቢያሰጠውም፥ ቅሉ ግን ዓለምን ከማቀራረብ አልቦዘነም፡፡ ታዲያ ዛሬ ዛሬ ለዓለም መቀራረብ እንደ ፈተና እየታየ ያለው ስደትና መጤ-ጠልነት ምድርን የሰው ልጆች መኖሪያ እንዳልሆነች ያሰኝ ጀምሯል፡፡ በእርግጥ ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ የተለያየ አይነት አቋም እንዳላቸው አይካድም፡፡