በሌላ ፕላኔት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ውኃ ተገኘ፡፡

ሀዋሳ፡ መስከረም 01/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሥነ ህዋ ተመራማሪዎች በአንዲት ፕላኔት ላይ ውኃ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ኢኢ በብሪታኒያ የመጀመሪያ የሆነውን 5 ጂ የሞባይል ኔትዎርክ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢኢ የተሰኘው ኩባንያ በብሪታንያ የመጀመሪያ የሆነውን 5 ጂ የሞባይል ኔትዎርክ ይፋ አድርጓል።

ኩባንያው 5ጂ የሞባይል ኔትዎርኩን ይፋ ያደረገው በታሜት ወንዝ ላይ በቀጥታ በሚተላለፈው የራፐር ስቶርምዜይ የሙዚቃ ድግስ ላይ ነው ተብሏል።

ይህ የ5 ጂ የሞባይል ኔትዎርክ መረጃዎችን በፍጥነት ለማውረድ ከማስቻሉ በተጨማሪ ፈጣን የኢንተርኔት አግልግሎት ለማግኘት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በአንድ ሲም ካርድ 5 ጂ ሞባይል ኔትዎርክ ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ማስተላለፍ  የሚቻል መሆኑም ነው የተገለፀው።

አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰወኑ ከተሞች ብቻ የሚሰጥ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎች አግልግሎቱን ለማግኘት አዲስ የሞባይል ቀፎ መግዛት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት