ሀዋሳ፡ ጷጉሜ 05/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያ በክረምት ወቅት የእብድ ውሻ በሽታ በስፋት እንደሚከሰት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዶክተር ባዬ አሸናፊ ተናገሩ፡፡

በሆስፒታሎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታችን የጠበቁ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው፡፡

ሀዋሳ፡ ጷጉሜ 01/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሆስፒታሎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ወቅታቸውንና ጥራታችን የጠበቁ እንዲሆኑ የጤና ሚኒስቴር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::

በሀገራችን በአሁን ወቅት የተከሰቱ የህብረተስብ ጤና አደጋዎችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
 
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሀገራችን በአሁን ወቅት የተከሰቱ የህብረተስብ ጤና አደጋዎችን በተለይም የችኩንጉኒያ፣ የኮሌራና፣ የፖሊዮ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉትን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
 
የችኩንጉኒያ ወረርሽኝን በተመለከተ
• ችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ችኩንጉኒያ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ ህመም ነው፡፡ የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ተከስቷል፡፡ በወረርሽኙም እስካሁን ድረስ ከ20,000 በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት የለም፡፡
• በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ 86 ፐርሰንት የሚሆኑት ቤቶች ወረርሽኙን የሚያስተላልፈው ትንኞች እጭ ተገኝቶባቸዋል
• ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች የተውጣጣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታው በመገኘት የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
• ወረርሽኙን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በክንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃል ተቋቁሞ በቅንጅት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የቤት ለቤት ርጭት፣ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የህክምና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማቶች የመስጠት ስራዎች ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡
• ማህበረሰቡ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዲችል ለሃይማኖት አባቶች፣አመራሮች፣ለማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም ለመገናኛብዙሃን ባለሙያዎች በአጠቃላይ ለ125 ሰዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
• ከዚህም ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለምላሽ አሰጣጡ የሚያገዙ የባለሙያ፣ የኬሚካል፣የመድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ለድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የ 1.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
• ይሁንና የተቆራረጠ ዝናብ የሚጥልበት ወቅት በመሆኑና በድሬደዋ የዝናብ ዉሃ ፍላጎት ከፍተኛ መሆን ይህም ለትንኟ መራባት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥር ወረርሽኙን በቀላሉ ለመቆጣጠር እንዳይቻል አድርጎታል፡፡
ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
• ሕብረተሰቡ ለትንኝ ንክሻ ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍን ልብስ መልበስ፣ የትንኝ መከላከያ ቅባት በቆዳ ላይ መቀባትና በሚተኙበት ጊዜ ሁሉ የአልጋ አጎበር በመጠቀም ራስን ከትንኝ ንክሻ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
• በዋናነት ማንኛውንም ለትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን፣ የወዳደቁ ውኃ የሚቋጥሩ ጎማዎችና ሌሎች ዕቃዎችን ማስወገድ፣ በየቤቱ የሚገኙ የተጠራቀመ የዝናብ ውሃ በማፋሰሰስና ቤትንና አካባቢን በትንኝ መከላከያ ኬሚካል በባለሙያ በማስረጨት ራሳቸውን እንዲከላከሉ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡
 
የኮሌራ ወረርሽኝን በተመለከተ
 በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ ወረርሽኝ በአብዛኛው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሶስት ክልሎች ላይ በሽታው አልፎ አልፎ እየታየ ነው፡፡
 በአሁን ወቅት ወረርሽኙ በኦሮሚያ ( በሻሸመኔ ወረዳ 15 ሰዎች ና ፈዲስ ወረዳ 20 ሰዎች) ፣ ሀረሪ ክልል በ6 ወረዳዎች 15 ሰዎች ና ደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማ 14 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን ሁሉም አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
 የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ማህበረሰቡ በዚህ ሳይዘናጋ አሁንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለሁ፡፡
 
የፖሊዮ ወረርሽኝን በተመለከተ
እንደሚታወቀው ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ በሽታ ) በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ቦህ ወረዳ አንጋሎ ቀበሌ በግንቦት ወር 2011ዓ.ም መከሰቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የተከናወኑ ተግባራት:-
 የፖሊዮ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም የህፃናትን የፖሊዮ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት በሱማሌ ክልል በአምስት ዞኖች (በዶሎ፣ጀረር፣ፋፋን፣ኖጎብና ኤረር) በሚገኙ 48 ወረዳዎች እንዲሁም 5 ተፈናቃይና 3 ስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ እድሜቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ከ 500,000 በላይ ህፃናት ክትባት ተሰጥቷል፡፡ በቀጣይም በነዚሁ ቦታዎች ቀድሞ ለተከተቡ ህፃናት ከመስከረም 5-8/2011 ዓ.ም የዘመቻ ክትባት የሚከናወን ይሆናል፡፡
 የመደበኛው ክትባትን ከማጠናከር አኳያ እንዲሁም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ ስለወረርሽኙ ምንነት ለሚዲያ ባለሙያዎችና ለሃይማኖት አባቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮገራም ተካሂዷል፡፡
 የድንበር ተሸጋሪ የፖሊዮ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ከሶማሌ ላንድና ፑንት ላንድ የጤና አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎ በጋራ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት