ስለ ድርጅቱ

የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብዙሃን መገናኛ ድርጅት በአዋጅ 87/97 ከተቋቋመበት ማግስት ጀምሮ ቀደም ሲል በባህል፣ ማስታወቂያና ቱሪዝም ቢሮ ስር እየተዘጋጀ ለክልሉ ህዝብ ሲሰራጭ የነበረውን “የደቡብ ንጋት” ጋዜጣን እና የመሳሪያ ተከላውና የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለስርጭት ዝግጁ የነበረውን የደቡብ ድምጽ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 100.9 በማካተት ተግባሩን ማከናወን ጀመረ፡፡ጋዜጣውን አሳትሞ ከማሰራጨት ባሻገር፣ የሬዲዮ ስርጭቱ በየእለቱ ለ3 ሰአት የሙከራ ስርጭት በማከናወን፣ በየእለቱም የሚዘጋጁ የቴሌቪዥን ዜናዎችን ለኢሬቴ ድ በመላክ ተግባሩን ማከናወን ቀጠለ፡፡ከጋዜጣ ቀጥሎ ለክልሉ ህዝብ እና መንግስት 2ኛው የብዙሃን መገናኛ መሳሪያ የሆነው የደቡብ ድምጽ ሬዲዮ ኤፍኤም 100.9 የካቲት23/1996ዓ.ም የክልሉ ር/መስተዳደር በነበሩት እና በኢፌዲሪ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በይፋ ተመርቆ ወደ መደበኛ ስርጭት አገልግሎት ተሸጋግሯል፡፡

የድርጅቱ ራዕይ፣ተልዕኮ፣ዓላማ እና እሴቶች

ራዕይ  (Vision)

የተጀመረውን የልማት የመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያፋጥኑ መረጃዎች በብቃትና ጥራት በማሠራጨት በ2020 ዓ.ም በክልሉ በመረጃ የበለፀገ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልዕኮ  (Mission)

ሕገመንግሥታዊና ዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን የጠበቁ ሕብረተሰቡን ያሳተፉ ወቅታዊ& ሚዛናዊ& አስተማሪና አዝናኝ መረጃዎችን እንዲሁም ፕሮግራሞችን በክልሉ የሥራ ቋንቋ፣ በብሔረ-ብሄረሰብ ቋንቋዎች በማስተላለፍ የክልሉን ሕዝብ ፖለቲካዊ& ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ሕይወት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ማገዝ፡፡