የገቢዎች ሚኒስቴር በነሃሴ ወር ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ፡፡

ሀዋሳ፡ መስከረም 04/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የገቢዎች ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት አመት በሰራቸዉ የንቅናቄ ስራዎች፣ የህግ ማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የህግ ማሻሸያ ስራዎች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።

27 ሚሊየን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ መድሃኒት ተያዘ፡፡

ሀዋሳ፡ መስከረም 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል እየሰሩት ባለው ስራ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በመያዝ ላይ ይገኛሉ።

 
የክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲትዩት የተጣለበትን ህዝባዊ ግዴታ እንዲወጣ ችግሮቹ መቀረፍ እንዳለበት ተገለጸ
 
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 29/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲትዩት የተጣለበትን ህዝባዊ ግዴታ እንዲወጣ ተቋሙ ያለበት የበጀት እጥረት መቀረፍ እንዳለበት በክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡
 
የአገር ውስጥ የስኳር ምርትን ወደ 4.8 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ እየተሰራ ነው
 
ሀዋሳ፡ ጷግሜ 01/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአገር ውስጥ የስኳር ምርትን ወደ 4.8 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

 
ዳቦ ቤቶች የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በህገወጥ መንገድ እስከ መሸጥ መድረሳቸው ተገለጸ
 
 
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበራት ጋር እያካሄደው ባለው የውይይት መድረክ ላይ በከተማዋ ያሉ ዳቦ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
 
በመድረኩ ለውይይት በወቀረበው ሰነድ ላይ እንደሰፈረው መንግስት ለህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ሲል የአንድ ዳቦ ዋጋ በ1 ብር 30 ሳንቲም ተምኖ ለዚህ የሚውል ስንዴን በድጎማ በ550 ብር እያቀረበ ይገኛል፡፡
 
ሆኖም ዳቦ ቤቶች ስንዴውን ገበያ በማውጣትና ‘ልዩ ስንዴ’ በማለት በ2 ሺህ ብር እየሸጡ 1 ብር 30 ሳንቲም የነበረ የዳቦ ዋጋ 3 ብር ድረስ ሲሸጥ እንደተደረሰበት በሰነዱ ላይ ቀርቧል፡፡
 
ከዚህ ባለፈ ዳቦ ቤቶች የተፈቀደላቸው ዳቦ እንዲያቀርቡ ቢሆንም ኩኪስ፣ ዶናት፣ ኬክና መሰል ምርቶችን በድጎማው ስንዴ አምርተው በመሸጥ ላይ እንደሚገኙም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
 
በዚህ መሰረት ቁጥጥር ሲደረግ በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት ሲሰሩ የነበሩ ዳቦ ቤቶች አርበኞች፣ ሮዛ፣ አፍሪካ እና ምስራቅ ዳቦ ቤቶች ብቻ መሆናቸውም ተያይዞ መገለጹን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡
የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት