የፈረንሳይ የእግር ኳስ መጽሄት የሚያዘጋጀው የ2019 የባሎንዶር እጩ ተመራጮችን ይፋ አደረገ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የፈረንሳይ የእግር ኳስ መጽሄት የሚያዘጋጀው የ2019 የባሎንዶር እጩ ተመራጮች ሰላሳ ያህል ተጨዋቾች ሲመረጡ አምና የአውሮፓ ሻምፒየስ ሊግ ባለድሉ የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ሰባት ያህል ተጫዋቾች በማስመረጥ ቀዳሚ ክለብ ሆኗል፡፡

የአውሮፓ ሻምፒየስ ሊግ ጫዎታዎች ዛሬ ምሽትም ቀጥለው ያካሄዳሉ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአውሮፓ ሻምፒየስ ሊግ ሶስተኛ የምድብ ጫዎታዎች ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፖ ከተሞች ከምድብ አንድ እስከ አራት ያሉ ክለቦች ይጫወታሉ፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከዓለም 7 ምርጥ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች አንዱ ሆኑ

ሀዋሳ፡ መስከረም 16/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬን ከዓለም 7 ምርጥ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች አንዱ ናቸው ብሏቸዋል፡፡

ፌደሬሽኑ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬን ጨምሮ ሌሎች 6 ምርጥ አሰልጣኞችን “የአለማችን ምርጥ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ” በማለት እውቅና ሰጥቷል፡፡

ከ7ቱ መካከል ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከአፍሪካ ብቸኛው ሆነዋል፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል በአሰልጣኝነት ቆይታቸው ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ገብረእግዚያብሔር ገብረማርያም፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋርን ጨምሮ በርካታ ዕንቁ አትሌቶችን አሰልጥነው ለውጤት አብቅተዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን

 

በዱሃ አስተናጋጅነት እየተደረገ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስደናቂ ሁነቶች ተፈጽመዋል

ሀዋሳ፡ መስከረም 19/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ )በዱሃ አስተናጋጅነት እየተደረገ ባለው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ አስደናቂ ሁነቶች ተፈጽመዋል፡፡
ለሃሩባ የሚሮጠው አትሌት ጆናታን ባስባይ የሀገሪቱን ሙቀት መቋቋም አቅቶት መም ላይ ይወድቃል፡፡ ታድያ ለአፍሪካዊቷ ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ የሚሮጠው ብሬማን ሳንካር ዳቦ ከቀሪ አትሌቶች ጋር ከሞፎካከር ይልቅ ሰብዓዊነት በልጦበት የተጎዳውን ወንድሙን አዝሎ እዲጨርስ ይረዳዋል፡፡
አትሌት ጆናታን ባስባይ በውድድሩ አንዳቋረጠ ተደርጎ ቢቆጠርበትም አልበገር ባይነቱ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ እንዲወደድ አድርጎታል፡፡ ሀገሩን ወክሎ ወደ ኳታር ያመራው ዳቦ 5000 ሜትሩን ከተሳተፉ አትሌቶች መቅደም የቻለው ያዘለውን ባስባይን ብቻ ነበር፡፡
ከሩጫው መጠናቀቅ በኋላ ከሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳቦ ’’በሰራሁት ስራ ሀገሬም ደስተኛ ናት፡፡ አኔም ውድድሩን ያሸነፍኩ ነው የመሰለኝ፡፡ በህይወት ዘመኔ ስደሰት የምኖርበትን ነገር በማድረጌ የጭንቅላት እረፍት ማግኘት ችያለው፡፡’’ በማለት ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡
የዚህ ውድድር ተሳታፊ የነበሩት ዳቦ እና ባስባይ ዛሬ በሚደረገው የ5000ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ላይ በመገኘት ይታደማሉ፡፡ በአንድ የመሮጫ መም የጀመረው ጓደኝነት በደም ከተሳሰረው ወንድማዊነት በልጦ ቀጣይ ሆኗል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ በ5000 ሜትር ኢትዮጵያዊያኖቹ አትሌቶች ጥላሁን ኃይሌ፤ ሰለሞን ባርጋ፤ ሙክታር አንድሪስ እና ሀጐስ ገ/ህይወት የፍጻሜ ውድድራቸውን ምሽት 3፡50 ላይ ያደርጋሉ፡፡ መልካም እድል ለአትሌቶቻችን፡፡
ዘጋቢ፡ አብርሃም ተስፋዬ

ሊዮኔል ሜሲ የዓመቱ የዓለም ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ
ሀዋሳ፡ መስከረም 13/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፊፋ የባርሴሎናውን ኮከብ ሊዮኔል ሜሲን የ2019 የዓለም ምርጥ ተጫዋች አድርጎ መርጧል።

Subcategories

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት