ሀዋሳ፡ መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቶች በህገ መንግሥት የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣትና የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አሳሰበ።
 
ምክር ቤቱ ይህን ያለዉ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ባለዉ አንደኛ መደበኛ ጉባኤዉ ነዉ።
የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሚ ኩርታ እንደገለጹት ምክር ቤቶች በህገ መንግሥት የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በተገቢው በማስፈፀም የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል።
 
ክልሉን ተወዳደሪ ማድረግና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዕድሎችን በመፍጠር ችግሮችን በመረዳት መፍትሄ እንዲያገኙ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የምክር ቤቶቹን አሠራር ለማሻሻል የህዝብ አስተያየት ከመሰብሰብ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ውስንነቶች መቅረፍ፣ በቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት ዙሪያ፣ በዞኖች ያለውን የጉባኤ መቋረጥን በዘለቂነት ማስተካከል እንደሚገባም በምክር ቤቱ አባላት ተጠይቋል።
 
ጉባኤዉ ከገመገመዉ የተቋማት አፈጻጸም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕቅድ ላይ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህግ ተገልጋዮች አፋጣኝ አገልግሎት በመስጠት ፍርድ ቤቶችን ወደ ተቀራራቢ ደረጃ ለማምጣት እንደሚሰራ ተገልጿል።
 
በተለይም የምድብ ችሎቶችና ተዘዋዋሪ ችሎትን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ የለውጥ መሳሪያዎችን በመጠቀም ስራዎችን ማቀላጠፍ እንደሚያስፈልግም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማርያም ጠቁመዋል።
 
የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የህዝብና የመንግሥት ሀብት ከብክነት ቀድሞ በመከላከል እንዲሁም ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ የክልሉ ኦዲተር ጀኔራል አቶ አስራት አበበ ገልጸዋል።
 
ምክር ቤቱ የክልሉን ምክር ቤት፣ የክልሉን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የቀጣይ ወራት ዕቅድና የምክር ቤቱን ያለፉትን ወራት አፈፃፀም ሪፖርት በጥልቅ በመገምገም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
ዘጋቢ፡ አሰግድ ሣህሌ - ከቦንጋ ጣቢያችን

Subcategories

ማህበራዊ ሚዲያ

//

www.srta.gov.et //www.srta.gov.et by www.srta.gov.et //