ኢጣሊያ ተቀባይ አጥተው በባህር ዳርቻ ለችግር የተጋለጡ ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነች፡፡
 
ሀዋሳ፡ መስከረም 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢጣሊያ መንግስት ከሌሎች አውሮፓ መንግስታት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ 82 ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኗል፡፡

በሳኡዲአረቢያ ሁለት የነዳጅ ማጣሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ፡፡

ሀዋሳ፡ መስከረም 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጥቃቱ የተፈጸመው በአነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሲሆን፤ አብቃይቅ እና ክሁራይስ በተባሉ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ አሳት መነሳቱ ተነግሯል፡፡

የመጽሐፍት ሥርጭትን ለማወቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡
 
ሀዋሳ፡ መስከረም 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2012 የትምህርት ዘመን በመላ አገሪቱ የመፅሐፍት ስርጭትን ለማወቅ የሚያስችል በቴክሎጂ የታገዘ አሰራር ተግባር ላይ እንደሚውል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የተለየ ጥያቄ ካልቀረበ በስተቀር በበጀት ዓመቱ መፅሐፍት የማተም ዕቅድ የለኝም ብሏል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ሀዋሳ፡ መስከረም 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአዲሱ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

 
የደቡብ ክልል መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቀነስ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡
ሀዋሳ፡ መስከረም 02/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ክልል መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቀነስ ብራይት ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ከተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

Subcategories

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት