አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕገ መንግሥት ረቂቅን አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕገ መንግሥት ረቂቅን አስመልክቶ በቤንች ሸኮ ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ በመደረግ ላይ ነው።የክልሉ ህገ መንግስት በ11 ምዕራፍና በ124 አንቀጾች የተዋቀረ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በሀገሪቱ 11ኛ ክልል ሆኖ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ በይፋ ይመሰረታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ ጦያር ይማም ከሚዛን ቅርንጫፍ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቤንች ሸኮ ዞን በተያዘው አመት ከ10ሺህ 400ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ በማልማት ከ2ሚሊዮን 500ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ግብ መያዙን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ አስታውቋል።መምሪያው በ2014 ዓ.ም የዞኑ የቡና ጥራትና ግብይትን በተገቢው ሁኔታ ለማስጠበቅና የመስኖ ልማት ስራ በተመለከተ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
Read more: በተያዘው አመት ከ10ሺህ 400ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ግብ ተይዟል
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የህብረተሰቡ ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የጠምባሮ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አስታወቀ።አቶ ታደሠ መኩሪያ የጠምባሮ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ በወረዳው ወባማ አካባቢዎችን በመለየት በየቀበሌያቱ ከሚገኙ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ወባን የመከላከል ሥራዎች በትኩረት እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።