ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ጋር ተወያዩ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ጋር በክልላዊ ሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የአመያ ኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የግቤ ውሃ 4ኛ ፕሮጀክት የሆነውን የአመያ ኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም ከፕሮጀክቱ ሰራተኞችና ከካምፓኒው ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአራት ተቃውሞ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸደቀ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአራት ተቃውሞ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር እየሰራች ነው - አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር በሚደረገው ጥረት ተግታ እየሰራች እንደምትገኝ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለፁ።

አርሶ አደሮችን አሰልጥኖ በመመዘን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ
ኤጀንሲው የተጭበረበሩ የብቃት የምስክር ወረቀቶችን ሰርዟል
ሀዋሳ፡ መስከረም 29/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) አርሶና አርብቶ አደሮች በማሰልጠን እና ተገቢውን ምዘና በማድረግ ብቃታቸውን ማረጋገጥና የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ አመለከተ። ኤጀንሲው የተጭበረበሩ የብቃት የምስክር ወረቀቶችን መሰረዙንም አስታውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት፤ ለዘመናት ሥር ሰዶ የቆየውን የሀገራችን የግብርና ዘርፍ የምርትና ምርታማነት ችግር ለመቅረፍ ከተለመደው የአሠራር ሂደት በተሻሻለ መንገድ መሥራት ያስፈልጋል። በመሆኑም የአርሶና አብርቶ አደሩን የሙያ ክፍተቶች እየለዩ የተቀናጀ ሥልጠና መስጠት የአርሶና አርብቶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ ሕይወቱን ማሻሻል እንደሚቻል አመልክተዋል።
ዳይሬክተሩ እንደሚሉት፤ የሀገሪቱ አርሶ አደር ምርታማነቱ እንዳይጨምር ካደረጉት ችግሮች መካከል የአርሶ አደሩ የአመራረት ክህሎት ማነስ፣ ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ገበያ ተኮር (ኮሜርሻላይዝድ) የሆነ አስተሳሰብ አለማዳበር ተጠቃሾች ናቸው። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በየደረጃው አርሶ አደሩን ጨምሮ በቂ የክህሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድግ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል።
እንደ አቶ ጌታቸው ማብራሪያ፤ የአርሶ አደሮችን የብቃት ምዘና ሂደት ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ በኩል በየደረጃው የሚገኙት ግብርና ቢሮዎችና ጽሕፈት ቤቶች ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላት ጋር ተቀናጅቶ የመሥራት እና የአመለካከት ችግሮች በመኖራቸው በሚፈለገው ደረጃ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አልተቻለም። በዚህ ሂደት አማራ፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ ክልሎችና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥልጠናውን ካልጀመሩት መካከል ተጠቃሾች ናቸው።
ትግራይ ክልል 23 ሺ አሰልጥኖ በማብቃት ቀዳሚው ሲሆን ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል 15 ሺ 991፣ አሮሚያ 9 ሺ 879 አርሶ አደሮችን አሰልጥነው አስመዝነዋል። ይሁን እንጂ የክልል አመራሮች በቁርጠኝነት ተግባሩን እየደገፏቸው እንዳልሆነም አቶ ጌታቸው ይገልፃሉ።
በሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬት አሰጣጥና አሠራር ዙሪያ ሀሰተኛና የተጭበረበሩ ሰርተፊኬቶችን በመጠቀም ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በክትትልና ሱፐርቪዥን የደረሰባቸውን በየማዕከላቱ እንዲሰረዙ ማድረጉን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንዳስታወቁት፤ በሀገሪቱ የዘርፉ አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑ እየታወቀ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አካላት በሕገወጥ ተሰማርተው ድርጅቶችን፣ ማህበረሰቡን እና ሰልጣኖችን በማታለልና በማጭበርበር ላይ መሆናቸውን በክትትልና ሱፐርቪዥን ማረጋገጥ ተችሏል።
“በዚህ የሌብነት ሥራ ተሳትፎ የነበራቸው በክልሎች 86 መዛኞች፣ 5 የምዘና ማዕከላት፣ 8 ሱፐርቫይዘሮች እና 86 ተመራቂዎች ላይ አስፈላጊው ሕጋዊ ርምጃ ወስደናል። 275 የተጭበረበሩ የምስክር ወረቀቶችም በየብቃት ማዕከላቱ አማካኝነት እንዲሰረዙ አድርገናል” ብለዋል አቶ ጌታቸው።
የፌዴራል ሙያ ብቃት ምዘና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ብርሃነመስቀል በበኩላቸው ድርጊቱ በዘርፉ የሚሰተዋሉ የክህሎት፣ የብቃት እና የአመለካከት ችግሮችን ለመቅረፍ  በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከመሆኑም ባሻገር ምርታማነትን ይቀንሳል ሲሉ አመልክተዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በየወረዳው ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በበቂ የተግባር ክህሎት ሰልጣኞችን ብቁ በማድረግ፣ የምዘና ማዕከላትን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል። በመሆኑም በራሳቸው የሚተማመኑ ብቁ መዛኞች በማሰማራት እና ብቁ ተመዛኞች በማፍራት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅርበት ተቀናጅቶ በመስራት የዘርፉን የሙስና ተጋላጭነት ማስቀረት እንደሚቻልም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ሲል ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

Subcategories

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት