መገናኛ ብዙሃን ለውጡ የፈጠረላቸውን ነፃነት በአግባቡ እየተጠቀሙ አይደለም ተባለ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 24/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሃገሪቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ለውጡ የፈጠረላቸውን ነፃነት በአግባቡ እየተጠቀሙ አለመሆኑን የብሮድካስት ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ የሩብ አመት አፈፃፀሙን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

በባለስልጣኑ ሪፖርት የመገናኛ ብዙሃኑ በተለይም በ2011 ዓ.ም ለውጡ በሚፈለገው የህግ መስመር የመስራት ክፍተት እንደተስተዋለባቸው ተመልክቷል፡፡

ተቋሙ የመገናኛ ብዙሃኑ ለሚፈለገው አሰራር ተገዢ እንዲሆኑ ያለውን ስልጣን ለመጠቀም የፋይናንስና የባለሙያ ችግር አለብኝ ብሏል።

ይሁንና መንግሥት ከልካይነትን በማስወገድና ለመገናኛ ብዙሃኑ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር አስቦ ፈጣን እርምጃዎች ከመውሰድ ቢዘገይም ኃላፊነት በጎደለው የአዘጋገብ ቅርፅ የብልሽት ስፋቱም በዛው ልክ እየጨመረ መጥቷልም ብሏል ባለስልጣኑ።

ሃገሪቱ ለገጠማት ችግር የጥቂት መገናኛ ብዙሃን ሚና የማረጋጋት ሳይሆን አባባሽ እንደነበረም ጠቁሟል።

ሆኖም ለችግሩ ብቸኛ መፍትሔ እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን መዝጋት የሚለው ባለመሆኑ ተቋማቱ የህግን መስመር እንዲከተሉ ብቻ የማድረግ ስራ መስራት እንደነበርም ጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም ይወሰድ የነበረው እርምጃ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ላይ ብቻ የተመሰረተ ስላልነበረ የተሻለ የእርምጃ አወሳሰድ ስርዓትን ለመከተል ሲባል ትዕግስት መመረጡንም ነው የገለፀው።

ይሁን እንጅ አሁን በማይሻሻሉት የመገናኛ ብዙሃን ላይ ወጥ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጿል። (ኤ.ቢ.ሲ)

በአፍሪካ ቀንድ የታየው መልካም የትብብር መንፈስ በመላው አፍሪካ ሊሰፋ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 13/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአፍሪካ ቀንድ የታየው መልካም የትብብር መንፈስ በመላው አፍሪካ ሊሰፋ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም UNDP ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የላቀ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 13/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ከደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ እርስቱ ይርዳ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በተወያዩበት ወቅት ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የላቀ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

በጋሞ ዞን የሞተር ጀልባ ሰጥሞ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን የሞተር ጀልባ ሰጥሞ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

Subcategories

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት