የቀድሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
 
ሀዋሳ፡ ዿግሜ 01/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቀድሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
 
ሮበርት ሙጋቤ ከየካቲት ወር ጀምሮ ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው አረጋግጠዋል።
 
ዚምባቡዌን ለረጅም ዓመታት የመሩት ሮበርት ሙጋቤ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በህዳር ወር 2017 ላይ ነበር በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው የተነሱት።
 
ሙጋቤ ከነጻነቷ ማግስት ማለትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1980 አንስቶ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲሁም በአውሮፓውያኑ ከ1978 አንስቶ ከስልጣን አስከተነሱበት 2017 ድረስ ደግሞ በፕሬዚዳንትነት መርተዋል።
ምንጭ፡ ቢቢሲ