ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 30/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአፍሪካ ላይ አተኩሮ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ላለው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጉባኤ በዚያው የሚገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ላይም በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዳሰጋቸው እና መንግስት ከመንግስት ጋር ውይይት አድርገው መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው ኢትዮጵያውያኑ ጠይቀዋል።

ጥቃቱ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ባይሆንም በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር ተወያይተው መፍትሄ እንደሚፈልጉም ነው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የገለፁት።

ሰሞኑን ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች የአፍሪካ አገሮች ዜጎችን ኢላማ ባደረገ መልኩ የተፈጸመውን ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ ተፈፅሟል።

የኢትዮጵያ መንግስትም በየደረጃው የሚገኙ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ባለስልጣናት ጠንካራ ክትትል በማድረግ በውጭ ዜጎች ላይ በተፈጸመው ድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር እንዲያውሉና ለህግ እንዲያቀርቡም መጠየቁ ይታወሳል።

ምንጭ፡ ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት