ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የእስራኤል ቆይታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ሃገራት ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በደቡብ ኮሪያ ቆይታቸው ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ በኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈርመዋል።

በጃፓን ቆይታቸውም ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ተወያይተው፤ በሃገራቱ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
የደቡብ ኮሪያ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላም ወደ እስራኤል በማቅናት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል።

በቆይታቸውም ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቨን ሬቭሊን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚህ ወቅትም ሃገራቱ በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶስቱ ሃገራት ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።