እስራኤል በዌስትባንክ ከያዘችው መሬት ውስጥ የተወሰነውን የራሷ የማድረግ መብት እንዳላት በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ

Category: የውጭ ዜና Published: Sunday, 09 June 2019 Written by Super User

እስራኤል በዌስትባንክ ከያዘችው መሬት ውስጥ የተወሰነውን የራሷ የማድረግ መብት እንዳላት በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በዌስትባንክ ከያዘችው መሬት ውስጥ የተወሰነውን የራሷ የማድረግ መብት እንዳላት በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ።

አምባሳደር ዴቪድ ፍሪድማን በዌስትባንክ አሁን ላይ በእስራኤል በቁጥጥር ስር ከሚገኘው መሬት ውስጥ ቴል አቪቭ የተወሰነውን የግሏ የማድረግ መብት እንዳላት ተናግረዋል።

ፍልስጤም በአሜሪካ የቀረበውን የሰላም እቅድ መቀበል አለባት ያሉት አምባሳደሩ፥ ዌስት ባንክን በከፊልም ይሁን በሙሉ ለፍልስጤም የመመለስ መብቱም የእስራኤል ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

የእርሳቸውን አስተያየት ተከትሎ ግን ፍልስጤማውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም በአምባሳደሩ ላይ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት እያሰበ ስለመሆኑ ገልጿል።

ንግግራቸውን ጠብ አጫሪ ነው ያለው መስሪያ ቤቱ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ስጋት ናቸውም ብሏል።

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Hits: 45
የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት