ናሚቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን በኢንተርኔት መረብ ልትሰጥ ነው፡፡
 
ሀዋሳ፡ መስከረም 02/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ተቀማጭነቱ ዊነድ ሆክ የሆነው የናሚቢያው ኮንስታንቲያ የግል ትምህርት ቤት እንዳስታወቀው በ2020 እ.ኤ.አ በናሚቢያ ሙሉ በሙሉ በበይነ-መረብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
 
ትምህርት ቤቱም ከናሚቢያ ትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ማግኘቱ ተገልጿል።
 
“የናሚቢያን የትምርት ጉድለት ማረም አልተቻለም በሚል የሚነሳውን ትችት በመቅረፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ላለፉት ሰባት አመታት ተሞክሮ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል “ያሉት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አማንዳ ሞርስች ናቸው፡፡
 
ይህም የትምህርት ጥራት በሁሉም ቦታና ጊዜ ማረጋገጥን ዒላማ ያደረገ ነው ያሉት አማንዳ ሞርስች፡፡
 
“ትምህርት ቤታችን በናሚቢያ እ.ኤ.አ በ2020 ቢጀምርም ተማሪዎች ኢንተርኔት ባለበት የትኛውም ስፍራ ወይም ሀገር ሆነው በማንኛውም የአንድሮይድ ሲስተም፣ በሞባይልና ኮምፒውተር አለያም ላፕ ቶፕ ተጠቅመው መተግበሪያ ማውረድ ሳይጠበቅባቸው መማር ይችላሉም“ ነው ያሉት።
 
ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች አገልግሎቱን ለማግኘት የመለያ ቁጥር 24/7 በማስገባት ትምርቱን በድምጽ፣ በምስልና ፈተናዎችን መውሰድ ይቻላል ነው የተባለው።
 
በፈተናውም 50 በመቶ ካመጡ ወደ ቀጣዩ ምእራፍ መሸጋገርና ውጤታቸውንም በፍጥነት እዛው ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል።
ተማሪዎች ፈተናም ሆነ መጽሀፍትን ማውረድ አይጠበቅባቸውም ሲሉ ሞርስች መናገራቸውን ሲጂቲኤንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።