ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በልደታ መናፈሻ አካባቢ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በልደታ መናፈሻ አካባቢ ችግኝ ተከሉ።

በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት ዛሬ በተከናወነው የችግኝ ተከላ የከተማ ውበትን የሚጠብቁ የዘንባባ ችግኞች ነው የተተከሉት።

በመላው ሀገሪቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በይፋ ባስጀመሩት ዘመቻ 4 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

 

በፍሬህይወት ሰፊው

የቅጂ መብት © 2019 ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት