የስቅለት በዓል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 09/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ዛሬ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በዝማሬ እና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች እየተከበረ ነው፡፡

በዛሬዋ ዕለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን የተቀበላቸው መከራዎች በእነዚህ የእምነት ተቋማት ይዘከራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የስቅለት በዓልን የሀይማኖቱ ተከታይ ምዕመናን በየአብያተ ክርስቲያኑ ተሰብስበው ቀኑን በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች እንደሚያከብሩ ይታወቃል፡፡

ዘንድሮ ዓመት እንዳለፉት ዓመታት የዕለቱ ሀይማኖታዊ ስርዓቶች በየአብያተ ክርስቲያኑ ምዕመናን በተገኙበት የሚይከበር ሰሆን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲሁም ስርጭቱን ለመግታት በወጣው አዋጅ ምዕመናኑ በቤተክርስቲያን ሳይሆን በቤታቸው ኃይማኖታዊ ስርዓቱን እንዲያከናውኑ ሆኗል፡፡

በቤተክርስቲያን ስርዓትና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ ጥቂት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በተገኙበት የስቅለት በዓል በደቡብ ክልል በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ፡ ኢያሱ ሽፈራው