የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የምግብና ንጽና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 08/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ዋይድ ሆራይዞን ፎር ችልድረን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ደርጅት አድርጓል፡፡

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርዕስቱ ይርዳው ድጋፉን በፅህፈት ቤታቸው ተረክበዋል፡፡

ዋይድ ሆራይዞን ፎር ችልድረን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ደርጅት ያደረገው ድጋፍ 1 ሚሊየን 140 ሺህ ብር ግምት ያለው ነው፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት ዋይድ ሆራይዞን ፎር ችልድረን የደቡብ ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አሰተባበሪ አቶ ካህሳይ ወልዱ ናቸው፡፡

አሰተባበሪው እንደገለፁት ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰው የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ 700 ሺህ ብር ግመት ያለው ቁሳቁስ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድጋፍ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የስንዴ ዱቄት፣ መኮረኒ፣ ዘይት፣ የንፅህና መጠበቂያ አልኮል ደጋፍ ለአቅመ ደካሞችና ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውል መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በማንኛውም ጉዳይ ከመንግስት ጎን በመቆም ድጋፋቸወን አጠናክሮ እንደሚቀጠል ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ዋይድ ሆራይዞን ፎር ችልድረን ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሌሎችም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ፋሲል ኃይሉ