የኮረና ቫይረስን ለመከላከል እንዲቻል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ገየቶ ጋራ እንዳሉት የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ሥራዎች ተጀምረዋል።

የኮንሶ ህዝብ ባህላዊ መጠጥ በጋራና በብዛት የሚከወን በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ እንዳይተላለፍ የግንዛቤ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

በሽታው እንዳይከሰት ለማድረግ ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ በበኩላቸው የኮንሶ ህዝብ በርካታ ባህላዊ እሴቶች የሚከውን በመሆኑና ይህም ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ የጥንቃቄ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በአብነትም የኮንሶ ህዝብ የለቅሶ ሥነ ሥርዓት ላይ መጨባበጥ ተለምዶአዊ ተግባር በመሆኑ ይህንን በማስገንዘብ ህዝቡ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶች ሊዘጋ ይገባል ብለዋል።
የህዝቡ ባህላዊ ክዋኔ እንደተጠበቁ ሆነው በጊዚያዊነት ግን ጥንቃቄ ላይ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ታሪኩ ለገሠ