የደቡብ ክልል ምሁራን በሆሳዕና ከተማ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው

ሀዋሳ፡ ጥር 07/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ክልል ምሁራን በሆሳዕና በሀዲያ የባህል አዳራሽ ምክክር በማድረግ ላይ ናቸው ::

የሙሁራን የምክክር መድረክ በንግግር የከፈቱ የደቡብ ክልል የዲሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ሞገስ ባልቻ ናቸው::

አቶ ሞገስ እንደተናገሩት ሙሁራን ነፃ ወይይት በማድረግ ለህዝብ ለሀገር የሚጠበቅባቸውን ሀሳቦችን ከወትሮ በበለጠ መልኩ ማመነጨት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀው በትልቅ አላፊነት ለቀጣይ መፍትሔ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አሳስበዋል::

በምሁራን ጥናታዊ ጽሑፍ በመቅረብ ላይ ሲሆን በቀጣይ በቀረበው ጽሑፍ ላይ ውይይት በመደረግ ላይ ነው::
የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀን እንደሚቆይ ከወጣው መርሃ-ግብር ማወቅ ተችሏል::
ዘጋቢ :ፋሲል ኃይሉ