የሀላባ ብሔር የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በቁሊቶ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል

 

ሀዋሳ፡ ጥር 03/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀላባ ብሔር የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በሀላባ ዞን በቁሊቶ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል።

 

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውና ካቢኔያቸው ወደ ከተማው ሲገቡ ደማቅ አቀባበል በማድረግ የተጀመረው በዓሉ የቡራንቲቾ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤትን የመመረቅ የዞኑ አተዳደር ህንጻ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ እና የሀላባ ቴሌቪዥን የመመረቅ ሥነ ሥርዓትም ተከናውኗል።

 

በዓሉ የኦሮሞ፣ ቀቤና፣ ማረቆ፣ ሲዳማና ሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች ታድመውበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

ዘገቢ፡ በእውነቱ ታደሰ