በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርዕቱ ይርዳው የተመራው ልዑክ ቡድን የሳጃ ሆስፒታልንና የሳጃ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኮሌጅን ጉበኘ

 

ሀዋሳ፡ ታህሳስ 20/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርዕቱ ይርዳው የተመራው ልዑክ ቡድን የሳጃ ሆስፒታልንና የሳጃ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኮሌጅን ጉበኝቷል፡፡

 

ልዑካን ቡድኑ በመጀመሪያ ጉብኝት ያደረገው በ2009 ዓ.ም ወደ መጀመያ ደረጃ ሆስፒታልነት ያደገውን ሳጃ ሆስፒታልን ነው::

 

የሳጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር በልሰቲ ታፈረ ጉብኝት በማድረግ ላይ ለሚገኘው ልዑካን ቡድን ስለሆስፒታሉ አጠቃላይ የስራ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡

 

በገለፃቸውም በሆስፒታሉ የባለሙያና የህፃናት ማቆያ ክፍል እጥረት መኖሩን አብራርተዋል፡፡ የተበላሹ ማሽነሪዎች ጥገና ባለሙያ ባለመኖሩ ተቋሙ ለአላስፈላጊ ውጪ መዳረጉን ተናግረዋል::

 

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ርዕቱ ይርዳው በውስጥ አቅም የተለያዩ ግብዓቶችን ለማሟላት የተደረገውን ስራ በማድነቅ የሀገር ሀብት የማመንጨት አቅሙ ሲያድግ ማሟላት እንደሚቻል ገልፀው የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል::

 

ቀጥሎ የተደረገው ጉብኝት ሳጃ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ሲሆን የተቋሙ ዲን አቶ ሙላት ጎጃም ሰለተቋሙ ማብራሪያ አድርገዋል::

 

520 ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በመሰራት ላይ መሆናቸውንና ኮሌጁ ወደ ፓሊ ቴክኒክ ማደግ እንዲችል ቢደረግ የሚል ሃሳብ አንስተዋል::

    

በተጨማሪም የጋርመንት ሰራን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተናግረው ገብያው የሚፈልገው ስልጠና ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ አሳስበዋል::

 

በቀጣይ ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በሳጃ ከተማ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ፡ ፋሲል ኃይሉ