በስልጤ ዞን በብልፅግና ፖርቲ አስፈላጊነት እና ቀጣይ ግቦች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

 

ሀዋሳ፡ ህዳር 30/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በስልጤ ዞን በብልፅግና ፖርቲ አስፈላጊነት እና ቀጣይ ግቦች ላይ ትኩረት ያደረገ የአመራሮች የግንዛቤ መድርክ እየተካሄደ ነው።

 

በመድርኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ውህደቱ የውስጥ ድርጅትን ብሎም ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ለማጠናከር፣ በህገ መንግስቱ የተቀመጡ አንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ መፍጠር እና አቅምና እውቀትን በማሰባሰብ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያሉባትን ችግሮችን መቅርፍን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

 

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ተመሳሳይ መድረኮች በውህደቱ ላይ በአመራሩ፣ በአባላትና በደጋፊዎች እንዲሁም በሕዝቡ ዘንድ የሚስተዋለውን ብዥታ ለማጥራት እንደሆነም ተናግርዋል።

 

ውህደቱን ተከትሎ በአፍራሽ ኃይሎች የሚነሱ ስጋቶችን ለማስወገድ አስተሳሰቡን ማጥራትና ውህደቱን በብቃት ይዞ ከግብ በማድረስ ህዝቡን ወደ ዋናው ተልዕኮ የሚያደርስ አቅም ያለው አመራር መፍጠርን ያለመ እንደሆነም አክለዋል።

 

በመድርኩም የኢህአዴግ የእስካሁን ጉዞና በየጉባኤዎቹ ውህደቱን አስመልክቶ የተደረጉ ውይይቶችና ጥናቶችን የዳሰሰ ጽሁፍ ቀርቧል።

 

ይህንን ተከትሎም ውህደቱ ላይ ባተኮረ ሰነድ ላይ የቡድን ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።

ዘጋቢ፡ በረከት ክፍሉ