ሀዋሳ፡ ህዳር 26/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የከምባታ ጠምባሮ ዞን አመራሮች በቃጫ ቢራ ወረዳ ሺንሺቶ ከተማ በሚገኘው የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ደም ለገሱ፡፡

 

በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ መኔዶን ጨምሮ ሌሎች የዞን እና የቃጫ ቢራ ወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

 

ደም መለገስ የሌላውን ሰው ህይወት ማዳንና መታደግ መሆኑንም አቶ አክሊሉ ተናግረው ዘርና ብሄር በመለየት ከመጠቃቃት ሁሉም ሰው በመቆጠብ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ መስራት እንደሚገባም ምክትል አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል፡፡

 

በደም ልገሳ ፕሮግራሙ አርባ ዩኒት ደም መሰብሰብ ስለመቻሉ ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ